የኦኤምኤን የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) ፖሊሲዎች በሁሉም የኦኤምኤን የስርጭት መድረኮች (ፕላትፎርሞች) ማለትም በመረጃ መረብ (ኦንላይን)ላይ፣ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን በኩል ለማሰራጨት እና ለመተላለፍ ለተዘጋጁ ፣ ለተሰጡ ፣ ለተገኙ ይዘቶች ሁሉ ይተገበራሉ ፡፡  እንዲሁም ለኦኤምኤን የሚሰሩ እና ወክለው የሚሰሩ ሁሉም ግለሰቦች ሁሉ ለፖሊሲው የሥነ ምግባር መስፈርቶች ይገዛሉ ፡፡

ኦኤምኤን ይህንን የፖሊሲ ሰነድ ያቀናበረው የኤዲቶሪያል ሰራተኞቹ በተናጥል ወይም በጋራ የሚያዘጋጁትን ይዘት መቆጣጠር እንዲችሉ፤ እንዲሁም አድማጮቹና ተመልካቾቹ ኦ ኤም ኤን እንደ ድርጅት ሙያዊና እና ማህበራዊ ኃላፊነት በተሞላው አኳኋን ለሕዝብ ጥቅም የሚሰጠውን አገልግሎት እንዴት እንደሚተገብር ለማስገንዘብ ጭምር ነው ፡፡

ዋና አርታኢው በኤኤምኤን ለተዘጋጀው እና ለተሰራጨው ይዘት የመጨረሻ የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) ስልጣን እና ኃላፊነት አለው ፡፡